Tuesday, January 21, 2014

ሰልፍ

   ሰልፍ በአገራችን በኢትዮጵያ ይዘቱ እና አላማዉ ይለያይ እንጂ ጥንትም እንደነበር በብዙ ደራሲያን ተፅፎ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ሰልፍ በእምየ ሚኒሊክ ዘመን ለሁለት አላማ ሲባል ይተገበራል፡፡አንደኛዉ ጦር ሰራዊቱ ወይም ወዶ ዘማቹ አገርን ከጠላት ወረራ ለመከላከል ወደ ጦር ግንባር ሲዘምት በራስ ተነሳሽነት በወኔ በፉከራ ፣ በሽለላ ፣ በቀረርቶ በመታጀበ የሚካሄደዉ ሰልፍ ሲሆን ፣ ሁለተኛዉ ደግሞ የቤተመንግስት ባለሙአሎች እና የንጉሱ አማካሪዎች ፣የጦር አለቆች ፣የቤተክህነት ሊቃዉንት ፣የህዝብ እንደራሴዎች ፣የጦር ሰራዊት አባላት ፣ተራዉ ህዝብ እና ሌላዉ ሌላዉም እንደየ ማዕረጉ ሆኖ (ተሰልፎ)  በአጋፋሪዎች አስተባባሪነት ከንጉሱ ግብር ለመብላት የሚደረገዉ ስለፍ ነዉ ፡፡ይህ ሰልፍ እንግዲህ የሚደርገዉ በንጉሱ ፊት ተገኝቶ የማር ጠጅ ለመጠጣት ፣ጮማ ለመቁረጥ  ፣የሊቃዉንቱን ቅኔ ዘረፋ ለመታደም ፣የአዝማሪን ጨዋታ ለማዳመጥ ወ.ዘ.ተ ሲሆን የጦር አለቆች እና ወታደሮች በፉከራ እና በቀረርቶ ንጉሱን ለማዎደስ እና ታማኝነትነን ለማሳየት አጋጣሚዉን ይጠቀሙበታል ፡፡ይህ እንግዲህ ሰባራ ሳንቲም የማይከፈልበት እና በንጉሱ ችሮታ ብቻ የሚከናዎን ነዉ፡፡ ከንጉሱ ግብር ለመካፈል የሚያስፈልገዉ ነገር ቢኖር እንደ መደቡ እና ማዕረጉ ተሰልፎ ወደ አዳራሽ መግባትና መግባት ብቻ ነዉ፡፡ ይህ እንግዲህ በአሁኑ ሰአት በየትኛዉም ቦታ የሌለ እና እንደ ተረት እየተወራ ያለ ጉዳይ ሆኖል፡፡

 ከዚያም ወረድ እያልን ስንመጣ በጃንሆይ የንግስና ዘመን ሰልፍ ወራሪ ጦርን ለመከላከል እና ግብር ለመብላት መሆኑ ቀረና በአብዛኛዉ ለተቃዉሞ ወደ መሆን ተሸጋገረ ፡፡ በዚህም የተነሳ ህዝቡ እንደወትሮዉ ንጉሱ  (ጃንሆይ) በተገኙበትም ሆነ በመንገድ ሲያልፉ ባለበት በየመንገዱ ዳር ተደርድሮ (ተሰልፎ)  ለጥ ያለ ሰላምታ መስጠቱን ትቶ አገዛዙን ተቃዉሞ መፎክር ይዞ አደባባይ ወጣ፡፡ ይሄ ዘመን በአገራችን በኢትዮጵያ ታሪክ የተማረዉ ክፍል ለሀገሩ መቆርቆር እና የስልጣን ይገባኛል ጥያቄ ያነሳበት ጊዜ ነዉ፡፡ በዚህ የጎዳና ላይ ሰልፍ ባብዛኛዉ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ  (የቀድሞዉ ቀዳማዊ ኀይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ) ተማሪዎች ንቁ እና ዋነኛ ተሳታፊዎችም መሪዎችም ነብሩ፡፡ ታሪከ ከማይረሳቸዉ የተቃዉሞ መሪዎች መካከል እንደነ ጥላሁንግዛዉ፣  ዋለልኝ መኮንን ፣ማርታ ( የዋለልኝ መኮንን የፍቅር አጋር) እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ ባለንበት ዘመን የምንኮንናቸዉም ሆነ የምናወድሳቸዉ አስመራሪዎቻችንም ሆኑ መሪዎቻችን እንዲሁም አገሪቱዋን በተለያየ አቅጣጫ የሚዘዉሩአት ሊቃዉንቶቻችን በሙሉ የዚህ ዘምን የሰልፍ ዉጤቶች መሆናቸዉን ልብይሉአል፡፡ 
ምን ያደርጋል ይህ ዘመን የተማሪዉ ተቃዉሞ   ሀ ብሎ የተጀመረበትም ቢሆን በምላሹ የሰልፍ መሪዎችን እና ሰልፈኞችን ሂዎት መቅጠፍ የተጀመረዉ በዚሁ ዘመን ነዉ፡፡ የጥላሁን ግዛዉ፣ የዋለልኝ መኮንን እና ማርታ ሂወት ያለፈዉ በዚሁ ሰልፍ ነዉ፡፡እርግጥ ነዉ ፍቅረኛሞቹ ዋለልኝ እና ማርታ አዉሮፕላን ለመጥለፍ ሲሞክሩ ቢገደሉም ፤መነሻዉ በጊዜዉ የነብረዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ነዉ፡፡ የዚህ ዘመን ሰልፍ ዉጤቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ባብዛኛዉ ለዚህም ትዉልድ ተርፈዉታል፡፡ ሌላዉን ትተነዉ የነኝህ ሰልፎች የዚያን ጊዜ ገጽታ በብቸኛዉ ብሄራዊ ቴሌቪዥናችን ለተለያየ አላማ በተለያየ ጊዜ ለእኛ ለዚህኛዉ ዘመን ወጣቶች ባለንበት ይደርሰናል፡፡ በተለይ በተለይ የቀድሞዉ ቀዳማዊ ኀይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተሰብስበዉ ለምን ለምን ሞተ  ና ማርታ ለምን ሞተች የሚሉትን መፎክሮች በህብረት ሲያዜሙ መስማተ በጊዜዉ ለነበሩት ሰዎች ትዝታና ቁጭትን ሲያጭር ለእኛ ለአሁን ዘመን ወጣቶች የሚሰጠን ትርጉም የተለየ መሆኑ የማየቀር ነዉ፡፡ ወጣም ወረደ የዚህ ዘመን ሰልፍ አላማ በጊዜዉ የነበረዉን ጨቁዋኝ ንጉሳዊ አገዛዝ ከስልጣን በማዉረድ በምትኩ አለም ሲያቀነቅንለት የነበረዉን የሌኒን ህብረተሰባዊነት (socialist, communist) የፖለቲካ ርዕዮተ-አለም (ideology) በኢትዮጵያችን ለመተግበር የተደረገ ትግል ነዉ፡፡ 
                               

       በንጉሱ ዘመን የተደረገዉ ሰልፍ የጊዜዉን ሰልፍ መሪዎች ሂወት ቢቀጥፍም የሁላ ሁላ አላማዉ ተሳክቶ ንጉሱን ከስልጣን አዉርዶ በምትኩ የህብረተሰባዊነት ፖለቲካ ርዕዮተ-አለም አቀንቃኝ የክርስትና ልጅ የሆነዉን ወታደራዊ አገዛዝ  (ደርግ) በዙፋን ላይ አስቀመጠ፡፡ በዚህኛዉ የአገዛዝ ዘመን ደግሞ የሰልፍ አላማዉና ዉጤቱ እጅግ እየከፋ መጣ፡፡ በጉአድ ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኀይለማሪያም የስልጣን ዘመን አደባባዮች በወታደሮች እና በተለያዩ ጦር መሳሪያ ተሸካሚ ተሸከርካሪዎች ሰልፍ ተለወጠ  (መስከረም ሁለት የሚከበረዉን የአቢወት ቀን ማስታወስ በቂ ነዉ)፡፡ ይህ እንግዲህ ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለዉን መፎክር ያስተናገደ ሰልፍ ነበር፡፡ይሁንና ወታደራዊ ደርግ ስልጣን ላይ  የወጣበትን አላማ ስቶ የብዙሀኑን የተማረ ክፍል ይሁንታ ባለማግኘቱ እና ፓርቲዎች በህቡዕ በመደራጀታቸዉ ፤ደርግ ያለምንም ደም የሚልዉን እንጉርጉሮ ክዶ በምትኩ ነጭ ሽብር  ፣ቀይ ሽብር በሚለዉ ዘመቻ ኢትዮጵያ በደም ጎርፍ ታጠበች፡፡ በዚህ የአገዛዝ ዘመን እንደ ንጉሱ ጊዜ አደባባይ ወጥቶ ለመቃወም የሚያስችል ህግም እድልም አልነበረም፡፡ ከበፊቱ በተለየ አገሪቱ በምታደርጋቸዉ የዉሰጥ እና የዉጭ እማያባራ ጦርነት የተነሳ ስልፍ ሁሉ ወታድራዊ መልክ ነበረዉ ይባላል፡፡ የአሁኑን ዘመን ስላማዊ ሰልፍ ልብ ባልልም የዚያን ጊዜ ዘመን ሰልፍ ግን ግራ እጅን ከፍ  አና  ዝቅ በማድረግ ይካሄድ  ነበር ይባላል፡፡ መፎክር በግራ አጅም ይሁን በቀኝ እጅ ለእኔ ልዩነቱ አይታየኝም፡፡ እንግዲህ በዚህ ዘመን ነዉ የዚህ ጽሁፍ አላማ የሆነዉ የሰልፍ አይነት የተጀመረዉ፡፡ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ከተቃዉሞ እና ከድጋፍ ሰልፎች ባለፈ ተራን ለመጠበቅ አስገዳጅ ተራ(ሰልፍ) የጀመረዉ፡፡


ደርግ በሚከተለዉ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ስርአት የተነሳ በከተሞች ዉስጥ የነበረዉ ህዝብ የምግብ ሸቃጣ ሸቀጦችን ለማግኘት ሲል በየህብረት ሱቆቹ በር ላይ አያሌ ሰአቶችን በሰልፍ ማሳለፍ ጀመረ፡፡ ድርቅ ባጠቃችዉ የአገሪቱ ክፍሎች የነበረዉን ገበሬ ያለፍላጎቱ በግዳጅ ሌላ ቦታ (በአብዛኛዉ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል) ለማስፈር አያሌ አድካሚ ሰልፎች አካሂዶል፡፡እጅግ የሚያሳዝነዉ የዚያን ጊዜ ሰልፍ ግን ሰዉን ወደ እስር ቤት አና ከስርቤት ወደ እስር ቤት በሚወስዱበት ጊዜ የሚካሄደዉ ነዉ፡፡ስዉ ያለጥፋቱ እና ወንጅሉ መታሰሩ ሳያንስ እንደ በግ በሰልፍ እየተነዳ ወደ ማጎሪያ ቤት መነዳቱ  ያሳዝናል፡፡ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ እጅግ አስከፊዉ እና አሰቃቂዉ ሰልፍ የሚፈጸመዉ ጉድጉአዳቸዉን ቆፍረዉ በጉድጉአዳቸዉ ፊት በተደረደሩ  (በተሰለፉ) ተረሻኞች ነዉ፡፡

   ይህ እንግዲህ በአጠቃላይ በአገሪቷ  የሚታየዉ ነባራዊ ሃቅ ነዉ:: እኔ እንግዲህ ብዙ ሺህ ጥራዝ ነጠቆች በየዓመቱ ከሚፈለፈሉበት አንድ አንጋፋ ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ነዉ የምማረዉ:: ስለዚህ በዚያም  ስላለዉ  የሰልፍ ዓይነት ለመናገር  ረዳት አያስፈልገኝም::  ከላይ ባነሳኋቸዉ የሰልፍ ዓይነቶች ላየ እኔሙሉ በሙሉ  የመሳተፍ   ግዴታዉ ባይኖርብኝም ፤ ነገር ግን በተማርኩበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ  በሚካሄዱት ሰልፎች ላይ ግን የመሳተፍ የዉዴታ ግዴታ ነበረብኝ::በዚያም ስላለዉ ሁኔታ ሳልጠቅስ ባልፍ ሃሳቤን የተጓደለ ያደርግብኛል::

   እንግዲህ እኔ በምማርበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ የተሰለፍኩበትን ቀን ከመቁጠር፤ ሰልፍ ያልተሰለፍኩበትን ቀን መቁጠር ሳይቀለኝ አይቀርም:: በዚህ ግቢ በቆየሁባቸዉ አመታት ዉስጥ ሰልፍ ያልተሰለፍኩት ለመተኛት፣ከግቢ ለመዉጣት እና በግቢዉ ዉስጥ ለመንቀሳቀስ ብቻ ነዉ ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም።ከዚህ በተረፈ ማንኛዉም ተማሪ አዲስ ተማሪ ሆኖ( fresh man) ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሲገባ ሻንጣ ለማስፈተሽ ከተሰለፈዉ ረጅም ሰልፍ አንሰቶ ፤ ወይ ተመርቆ ወይም ተባሮ( ተጭሮ) ከግቢዉ እስከሚለቅ ድረስ የማይሰለፍበት ቀን ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ:: ቀን በቀን ለመመገብ በየካፍቴሪያዉ ሰልፍ ፣ በየሴሚስተሩ ለመመዝገብ በየፋኩሊቲዉ እና በየዲፓርትመንቱ በር ላይ ሰልፍ ፣ በመዝናኛ ማእከላት (tv room) ኳስ ለማየት ሰልፍ ፣ ሻዉር ለመዉሰድ ሰልፍ፣ ወደ ፈተና አዳራሽ ለመግባት ሰልፍ፣የተበላሸ ዉጤት ለማስተካከል ሬጅስትራር በር ላይ ረጅም ሰልፍ፣ በመመገቢያ አዳራሽ ዉስጥ ሻይም  ሆነ ዉሃ ለመቅዳት ሰልፍ፤ ቦታ ተገኝቶ በልተዉ ከወጡም በኋላ ቢሆንም እጅን ለመታጠብ መሰለፍ ግድ ነዉ።በሲኒማ ቤት ዉስጥ የሚታዩ ፊልሞችን ለማየት ከፈለጉም  በብቸኛዉ የመመረቂያ አዳራሽ  በር ላይ ከአንድ ሰዓት በላይ መሰለፍ የማይቀር መሆኑን አምነዉ መሆን አለበት። ከዚህ በመነሳት አንድ የዩንቨርሲቲ ተማሪ ለአንድ ቀንም ቢሆን ሰልፍ አልተሰለፍኩም ካለ አልተመገበም፣ አልጠጣም፣ ገላዉን አልታጠበም፣ በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስኳቸዉን ዩንቨርሲቲዉ የሚሰጠዉን አገሎት አልተጠቀም ማለት ነዉ።

         ይህ የዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ ከመለመዱየተነሳ ተማሪን የሚያስጨንቅም ሆነ የሚያበሳጭ አይደለም። ተማሪዉ ሰልፉ እጅግ የበዛ መስሎ ከተሰማዉ ሰልፉ ቀለል የሚልበትን ሰአት ጠብቆ ለመምጣት ይገደዳል። በተረፈ የሰልፍ ሰዓቱን በ ወሬና በጨዋታ ለማሳጠር የሚጥረዉ ይበዛል። ከዚህ ሌላ አማራጭ የለዉም። ከተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ዉጭ ለመመገብ ቢያስቡም እዚያም ቢሆን ቆመዉ አይሰለፉ እንጅ ተራ መጠበቅ ያለ ነዉ።ይህ ሰልፍ ሳስበዉ ተማሪዉ ከዩነቨርሲቲ ተመርቆ ሲወጣ የሚጠብቀዉን የሰልፍ አይነት እንዲለምድ ታስቦ የሚሰጥ የሰልፍ ስልጠና ይመሰለኛል።

      በተለይ በመመገቢያ አዳራሽ ሰልፍ ላይ በአንድ ወቅት አንድ ገጠመኝ አለኝ።የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለሁ፤ አንድ ስራ የሚበዛበት አስተማሪያችን  ከጥዋቱ 12፡30 እስከ  2፡30 ሊያስተምረን ተስማማን፡፡ታዲያ በተስማማንበት ቀን ለመማር ወደ ክፍል ከመግባታችን በፊት ቁርስ ለመብላት ካፍቴሪያዉ በሚከፈትበት ሰዓት ( ከጠዋቱ 12፡00)  በጣት የምንቆጠር የአንድ ዲፓርትመንት ተማሪዎች  ወደ ተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ (ካፌ) አመራን።ይህ እንግዲህ በአጠቃላይ በአገሪቷ  የሚታየዉ ነባራዊ ሃቅ ነዉ:: እኔ እንግዲህ ብዙ ሺህ ጥራዝ ነጠቆች በየዓመቱ ከሚፈለፈሉበት አንድ አንጋፋ ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ነዉ የምማረዉ:: ስለዚህ በዚያም  ስላለዉ  የሰልፍ ዓይነት ለመናገር  ረዳት አያስፈልገኝም::  ከላይ ባነሳኋቸዉ የሰልፍ ዓይነቶች ላየ እኔሙሉ በሙሉ  የመሳተፍ   ግዴታዉ ባይኖርብኝም ፤ ነገር ግን በተማርኩበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ  በሚካሄዱት ሰልፎች ላይ ግን የመሳተፍ የዉዴታ ግዴታ ነበረብኝ::በዚያም ስላለዉ ሁኔታ ሳልጠቅስ ባልፍ ሃሳቤን የተጓደለ ያደርግብኛል::

   እንግዲህ እኔ በምማርበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ የተሰለፍኩበትን ቀን ከመቁጠር፤ ሰልፍ ያልተሰለፍኩበትን ቀን መቁጠር ሳይቀለኝ አይቀርም:: በዚህ ግቢ በቆየሁባቸዉ አመታት ዉስጥ ሰልፍ ያልተሰለፍኩት ለመተኛት፣ከግቢ ለመዉጣት እና በግቢዉ ዉስጥ ለመንቀሳቀስ ብቻ ነዉ ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም።ከዚህ በተረፈ ማንኛዉም ተማሪ አዲስ ተማሪ ሆኖ( fresh man) ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሲገባ ሻንጣ ለማስፈተሽ ከተሰለፈዉ ረጅም ሰልፍ አንሰቶ ፤ ወይ ተመርቆ ወይም ተባሮ( ተጭሮ) ከግቢዉ እስከሚለቅ ድረስ የማይሰለፍበት ቀን ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ:: ቀን በቀን ለመመገብ በየካፍቴሪያዉ ሰልፍ ፣ በየሴሚስተሩ ለመመዝገብ በየፋኩሊቲዉ እና በየዲፓርትመንቱ በር ላይ ሰልፍ ፣ በመዝናኛ ማእከላት (tv room) ኳስ ለማየት ሰልፍ ፣ ሻዉር ለመዉሰድ ሰልፍ፣ ወደ ፈተና አዳራሽ ለመግባት ሰልፍ፣የተበላሸ ዉጤት ለማስተካከል ሬጅስትራር በር ላይ ረጅም ሰልፍ፣ በመመገቢያ አዳራሽ ዉስጥ ሻይም  ሆነ ዉሃ ለመቅዳት ሰልፍ፤ ቦታ ተገኝቶ በልተዉ ከወጡም በኋላ ቢሆንም እጅን ለመታጠብ መሰለፍ ግድ ነዉ።በሲኒማ ቤት ዉስጥ የሚታዩ ፊልሞችን ለማየት ከፈለጉም  በብቸኛዉ የመመረቂያ አዳራሽ  በር ላይ ከአንድ ሰዓት በላይ መሰለፍ የማይቀር መሆኑን አምነዉ መሆን አለበት። ከዚህ በመነሳት አንድ የዩንቨርሲቲ ተማሪ ለአንድ ቀንም ቢሆን ሰልፍ አልተሰለፍኩም ካለ አልተመገበም፣ አልጠጣም፣ ገላዉን አልታጠበም፣ በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስኳቸዉን ዩንቨርሲቲዉ የሚሰጠዉን አገሎት አልተጠቀም ማለት ነዉ።
         ይህ የዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ ከመለመዱየተነሳ ተማሪን የሚያስጨንቅም ሆነ የሚያበሳጭ አይደለም። ተማሪዉ ሰልፉ እጅግ የበዛ መስሎ ከተሰማዉ ሰልፉ ቀለል የሚልበትን ሰአት ጠብቆ ለመምጣት ይገደዳል። በተረፈ የሰልፍ ሰዓቱን በወሬና በጨዋታ ለማሳጠር የሚጥረዉ ይበዛል። ከዚህ ሌላ አማራጭ የለዉም። ከተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ዉጭ ለመመገብ ቢያስቡም እዚያም ቢሆን ቆመዉ አይሰለፉ እንጅ ተራ መጠበቅ ያለ ነዉ።ይህ ሰልፍ ሳስበዉ ተማሪዉ ከዩነቨርሲቲ ተመርቆ ሲወጣ የሚጠብቀዉን የሰልፍ አይነት እንዲለምድ ታስቦ የሚሰጥ የሰልፍ ስልጠና ይመሰለኛል።

      በተለይ በመመገቢያ አዳራሽ ሰልፍ ላይ በአንድ ወቅት አንድ ገጠመኝ አለኝ።የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለሁ፤ አንድ ስራ የሚበዛበት አስተማሪያችን  ከጥዋቱ 12፡30 እስከ  2፡30 ሊያስተምረን ተስማማን፡፡ታዲያ በተስማማንበት ቀን ለመማር ወደ ክፍል ከመግባታችን በፊት ቁርስ ለመብላት ካፍቴሪያዉ በሚከፈትበት ሰዓት ( ከጠዋቱ 12፡00)  በጣት የምንቆጠር የአንድ ዲፓርትመንት ተማሪዎች  ወደ ተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ (ካፌ) አመራን።

.                 ።።።።።።።።ይቀጥላል።።።።።።።።።።።።።።

Wednesday, January 1, 2014

በሃሳቤ ቀርጨ ስዬ ካስቀመጥኳት

ከልጅነት ፍቅር ከነቂም አይዙ
ጥቅም  አይፈልጉ
ነግቶ አይጠገቡ
በሆነዉ ባልሆነዉ ካልሆነዉ ብስጩ
አለም ሁሉ ለእሱ ገነት ከምትመስለዉ
ትንሽ ትዝታ  አለኝ በልቤ ቦታ አለዉ። 

ደግሞም ከበሰለዉ ከሚያመዛዝነዉ
ይህ ይበልጥ ያ ይበልጥ ብሎ ከሚመርጠዉ
ለጊዜያዊ ስሜት ቅድሚያ ከሚሰጠዉ
ቆሻሻ ብስባሽ ሀጢያት ከለበሰዉ
ባፈቀረዉ ልብ ዉስጥ ቅናት ከሚረጨዉ
መክዳት መሸዋወድ ርስቱ ከሆነዉ
በከንፈር በደረት እንዲሁም በዳሌ ከሚፈራርሰዉ
ከአዋቂዎች ፍቅር ትንሽ ቀምሻለሁ።
ግን በአሁኑ ሰአት
በሃሳቤ ቀርጨ ስዬ ካስቀመጥኳት
ያለኝን ሁሉ ልሰጣት ላወርሳት ከምጠብቃት
ስተኛ ከጎኔ በትራሴ ምትክ  ተኝታ ከማቅፋት
የግራ ደረቴን ከምትንተራሰዉ
የልቤ ትርታ ሙዚቃ ከሆናት
ጸጉሯን እያያሻሸሁ የኔነሽ ከምላት
ንጉሴ ስትለኝ  ቀን ሌት ካነገስኳት

ማታ በጨረቃ ከደጅ ቁጭ ብዬ
ባሳብ የሳልኳትን  የምወዳትን ልጅ  ከሃሳቤ አምጥቼ
ከጎኔ አስቀምጬ
ዘመም አርጋ አንገቷን አንገቴ ስር ገብታ
ሙቀቴን ሰጥቻት ሙቀቴን ፈልጋ
እየተደባበስን
በለሆሳስ ድምጸት እያንሾካሾክን
ፍቅር ስናወራ
ፍቅርን ስንበላ
በእጇ እየጠቆመች ሽቅብ ለጨረቃ
ዉዴ እወድሃለሁ ማሬ አፈቅርሃለሁ
እማኝ ወይ ምስክር ትሁነኝ ጨረቃ
ብላ ስታበቃ፤
እኔም ብዬ ሳልል ድምጽ ሳላወጣ
የፍቅሬን ጥልቀት የመዉደዴን ርቀት ልናገር ስቃጣ
ከምታስቸግረኝ  ሙቀቷ ሳይለቀኝ አካሏ እየጠፋ፤



ደግሞም አመሻሽ ላይ በመንገድ እየሄድኩ
በእግሬ የድንጋይ ጓል ወደፊት እያጓንኩ
እጄ ኪሴ ገብቶ እየተንጎራደድኩ
በከፊል ብርሃን  ዘንባባ እየታከኩ፤
ከወጪ ወራጁ ከተመላላሹ
ወይ የሚዋደዱ ወይ የሚወሻሹ
ላይሸዋወዱ የሚሸዋወዱ
በአርቴፊሻል  መዉደድ  በኮንትራት ፍቅር  የሚወላገዱ
ጥንዶች ያየሁ እንደሁ ተቃቅፈዉ ሲሄዱ
ያቺን ባሳብ ሸራ በመኞቴ ቀለም የሳልኳትን ወጣት
ወገቤን ጨምድዳ ስትይዘኝ አየኋት
ቀኝ እጄን በአንገቷ  እያመላለስኩኝ
በርምጃችን መሃል ሰገፋት ስትገፋኝ
በወጋችን መሃል አንዳንዴ  ስትመታኝ
ሂድ !!! ዉሸታም ስትለኝ
ለጊዜዉ አኩርፋ  ወዲያዉ ስትስቅልኝ
ባሳቤ ሸራ ላይ እያለሁኝ ስያት
ከጎኔ ሳትኖረ ከልቤ አስቀምጫት
ምኞቴ ቀለሙ ሳያልቅ ሳይነጥፍ
እያመለጠችኝ እንደማትያዝ ወፍ
ሳላያት  አሷን   ሳላገኛት  በዉኔ 
አምላክ አደራህን  አትለፍ  ሂወቴ 
                           የማይሰጠኝ ከሆን የማይቸረኝ እሷን
                           ጌታ ጌትነቱ ፍቅር መቼ ሊሆን
                           እያልኩኝ እያሰብኩ
                           በቀን እየታመምኩ
                           እያየሁኝ  ቅዥት
                           ለምን እያፈቀርኩ አወራለሁ ዉሸት
                                                          ታህሳስ 6 2006
                                                          አዲስ አበባ

                                        እዮብ መርሻ

Friday, December 27, 2013

ይቅርታሽን ብዬ

             ይቅርታሽን 

እንዴት ሳላስቀይም  እንዴት ሳላስከፋሽ
ለቁጣ የሚያደርስ በደል ሳልበድልሽ
ለመጥፎ ነገር አንዴም ሳላስብሽ
ስምሽን ሳልጠራ ለሰዉም ሳላማሽ
ከልቤ  አዉጥቼ  አፌ ሳላደርስሽ
የሚያስከፋ ነገር ቃል ካፌ ሳይወጣ፣
ይቅርታሽን ብዬ  አደባባይ ልዉጣ?
          እንኳን ያጠፋ ሰዉ  ፍቅርን የበደለ፥
          ንጉስ ይቅር ይላል  ፍርድ ካጓደለ፤
          ስሜት የሚያስቆጣ የሚያስከፋ  ነገር
          በልቡ ያሰበ  ካፉ ያመለጠዉ፥
          ፍቅሩ እንዲሰነብት
          ይቅርታ መጠየቅ  ይሆናል ግዴታዉ፤

ጡር ይሁን  አልልም  ጡር አይድረስብሽ
ግፍ  ነዉም  አልልም ግፍ አይሁንብሽ
ልትዋሽ የማትችይዉ  እዉነቱን የሚያዉቀዉ
                                ህሊናሽ ይዉቀስሽ።


                                                  ታህሳስ 1 2006
                                         አዲስ አበባ
                                         እዮብ መርሻ

Friday, December 20, 2013

ከወገብሽ በታች ልታንበረክኪ

ለእኔ መስሎኝ እንዲያ ስትንሰቀሰቂ
እጅሽን ዘርግተሽ አምላክሽን ስጠሪ
ማጥመድሽ ነዉና ከልቤ ልትገቢ
ከወገብሽ በታች ልታንበረክኪ
እኔ ጋ አልተሳካም ሌላ ሰዉ ፈልጊ
ከአእምሮሽ አስወጪኝ ከጎኔ ራቂ::



                                      ታህሳስ 2000 ዓ/ም
                                      ድሬዳዋ

                                      እዮብ መርሻ

Thursday, December 19, 2013

እኔስ ላንቺ ነኝ ስንተኛሽ?

ንኛዉ ነዉ ስንተኛሽ?
ሳትደብቂ ሳትዋሽ
የቱን ወደድሽ
ማን ? ደላሽ
ሁሉን ነገር ያሳየሽ
የተዳራሽ ያስተኛሽ
የስሜትሽን የቸረሽ
ፍላጎትሽን ያሟላልሽ
የተላፋሽ ያዝናናሽ
ፍቅር በጣም የሰጠሽ
ቀጭኑ ነዉ ረዥሙ
ማንኛዉ ነዉ? ስንተኛሽ?
ያስቀመጥሽዉ በልብሽ
የተሳለዉ በአእምሮሽ
በሰዓታት መዉደድሽ
ጊዜ ቀንቶት የታደለዉ
ዛሬ ተራዉየደረሰዉ
እሱ ማን ነዉስንት ቁጥሩ
ያስጎመዠሽ ዉበት ብሩ
የተመቸሽ ትኩስ ፍቅሩ
                      እኔስ ላንቺ ነኝ ስንተኛሽትላንትና የወደድሽኝ
                      ያለ ቢጫ ቀይ ብለሽኝ  ዛሬ ደግሞ የሸኘሽኝ
                      አዲስ ሌላ ያልዳበስሽዉ
                     ያላወቅሽዉ ያልቀመስሽዉ
                     ያ የዛሬዉጣፋጭ ማርሽ
                     የምተፊዉ ነገ መሮሽ
                     እንዲገባ አሁን ከጂሽ
                    ቶሎ ፈጥነሽ ተሽቀዳድመሽ
                    ምጣጭሽን ወዲያ ተፍተሽ
                    ትኩሱን ማር እየላስሽ
                   ብትገፊበት  በዚህ ስራ
እኔም ደግሞ ተራዬ አልፎ
ይህ  ሁሉ ህዝብ ተሰልፎ
ብጠባበቅ ሌላ ተራ
ጊዜዉ ደርሶ እስክጠራ
እንደገና ብፈልግሽ  ፊት ባሳይሽ
የአዳምን ዘር ሁሉ ቀምሰሽ
መላላሱ መታገሱ ሳያጠገብሽ
ልታኝኪኝ ልትበይኝ ደግሞ ዞረሽ ትመጫለሽ
የሂዋን ዘር መቼም አንቺ ሀፍረት የለሽ::

                                      እዮብ መርሻ እና ዉብሸት አሰፋ ዶ/ር

                                       ሐረር  1999 ዓ/ም

አጨስሽ

አዉቅሻለሁ አንቺን ከሁሉም በፊት
አናዳጅ አቃጣይ ዉብ አለብላቢት
ምን አፍ አካፈተሽ በዉድቅት ሌሊት
ሰዎች አጨስሽ አሉኝ ነገሩኝ ያዩት::

                                                          ሰኔ  1999 ዓ/ም
                                                          ሐረር
                                                          እዮብ መርሻ

Friday, December 13, 2013

"እኔ ፍቅር ላይ ነኝ,,,"

"እኔ ፍቅር ላይ ነኝ,,,"
የወሬ ማድመቂያ  አደረጉኝ  አሉ
የኔን መዉደድ ማፍቀር  ሲያነሱ ሲጥሉ
ከንቶኔ ከእከሊት ይሆናል እያሉ
ሲያጋቡኝ ሲያፋቱኝ  ቀን ይመሻል አሉ
ሲበጠስ ሲቀጠል ሲነፈስ  ሲበጠር
ሲቦካ  ሲጋገር
ስሜ እንዲህ የዋለዉ
ያለአንዳች  አይደለም  ያለ ምክንያት
እሳት በሌለበት ጢስ ኧረ ከወዴት
                                አልክድም አልዋሽም  አላልኩም  ሀሰት
                                ይስሙትም  ይወቁት  ሁሉንም  ይረዱት
                                ለምን ጊዜ ያጥፉ  ለምንስ ያስቡት
                                በየወሬዉ መሃል  ስሜን  ለምን ያንሱት
                                ስጋዬን ቀን ከሌት ለምንስ ያላምጡት
እውነት ነዉ ልክ ነዉ  ኧረ አልተሳሳቱም
አዎ ፍቅር ላይ ነኝ  ለማንም አልክድም
መቼም ከማትርቀኝ  ከማትለወጥ
ከምትመጣልኝ  ብቻዬን  ስሆን
ከተቀመጠችዉ  ከሀሳቤ ስር
ከቀዝቃዛዉ ደሜ  ከልቤ  ሰፈር
እኔ  ፍቅር ላይ  ነኝ “ከትዝታ” ጋር።
                                        

                                                    ህዳር 30 ፥2006አዲስ  አበባ
                                                              እዮብ መርሻ



Thursday, December 12, 2013

“አይኗ አይኔን እያየዉ᎐᎐᎐᎐᎐”

    “አይኗ  አይኔን  እያየዉ᎐᎐᎐᎐᎐”
ቀጥራኝ  ስጠብቃት  የዉሃ ላይ ሽታ የሆነች እንደሆን
ስልኬን ሳታነሳ የቀረች እንደሆን
ለመልዕክቴ  ምላሽ የነፈገችኝ ቀን
ከአከሌ  ጋር  ሆና  አየናት ያሉኝ ቀን
ደግሞም አግር ጥሎኝ በአይኔ  በብረቱ
ከሌላ ጎበዝ ጋር ያየሁአት አንደሆን            
               እንገበገባለሁ  እብከነከናለሁ
               የመከዳት ስሜት   የመከፋት ስሜት  በፊቴ  አሳያለሁ
              ፊቴ ተኮማትሮ
              ከሰል መስሎ ጠቁሮ
              ዝናብ የቋጠረ ደመና እመስላለሁ
              ብቻዬን አጉተመትማለሁ
              ጨርቁን እንደጣለ  እንዳበደ  ሰዉ
              እጄን ወዲያ ወዲህ አወረጫጫለሁ
              ቆይ ትምጣልኝ ብዬ እጅግ እዝታለሁ
              እጄን  በእጄ ቡጢ                    
              ደግሜ ደግሜ ደግሜ  እመታለሁ::

ብርሃኑ ቀኔ  በእሷ ጨልሞብኝ
እሸሽበት መንደር
እገባበት ጉድጓድ እጠፋበት ሰፈር፣
ካሳቤ ጠፍቶብኝ
ደግሞም ቅናት ቢጤ  እያንጨረጨኝ
ደም  ደም አሸትቶ   እያቀጣጠለኝ
ሃሳብ ሆዴ  ገብቶ  እያብከነከነኝ፣

የመጨረሻ  ነዉ  ዛሬስ በቃ እላለሁ
ትምጣና  እምላትን  እኔ  አዉቅላታለሁ
የት ነበርሽ?? ከማን ጋር?? እያልኩ አጣድፋታለሁ
ከእግሯ እስከ ራሷ እወርድባታለሁ      
እንዲህ ነሽ እንዲያ  ነሽ እያልኩ  እላታለሁ
ያየሁባትንም የሰማሁትንም
ዘክዝኬ  ዘክዝኬ  አወራላታለሁ
ንዴቴን  በሙሉ  አውጣባታለሁ
አልያም ሰድቢያት  ባለችበት  ቆማ ትቻት  አሄዳለሁ
ሁለተኛ አይንሽን አንዳላየዉ ብዬ አባርራታለሁ
         ብዬ አደነፋለሁ  !!!
         ብዬ አገዘታለሁ !!!


ታዲያ ስትመጣ  ስትቆም  ከፊቴ
አይኗ  ሲስለመለም  አያየሁት ባይኔ
ችግሩ ከማን  ነዉ  ከሷ  ነዉ ውይ  ከኔ
ብዬ አጠይቃለሁ  ከጋለዉ ስሜቴ  ቆራረጣለሁ
ባጠመደኝ አይኗ  ወኔዬ ተሰልቦ በረግጋለሁ
ጥፋቱ የኔዉ ብዬ  መለሳለሁ።
                     ግን  ምን  አረገችኝ  ምስኪን  ናት ፣ ቆንጆ ናት
                     በዚህ ላይ ደግሞ ያለኔስ  ማን አላት
                     ደግሞም  የሰማሁት ያየሁት በሙሉ
                     እዉነት መሆኑንስ  በምን አዉቃለሁኝ
                     እንድያዉ ነዉ ዝምብዬ  ሷን የኮነንኩኝ
                                                    ብዬ  ሞኛለሁኝ።
                 

አዬ ድንፋታ አቴ   አዬ  መንቆራጠጥ
መንቸርጨር  መቃጠል ማለት ቁጭ  ብድግ
ለዚሁ  ነዉ ለካ
አጇ  አጄን  ፈልጎ አስኪነካ
ጥርሷ  በፈገግታ  በጥልቅ  አስኪፈካ
አይኗ  ካይኔ  ጋራ አስኪያወካ
ከንፈሯ ከንፈሬን  አስኪሄድ  ፍለጋ።

                     ታዲያ ንዲሁ  አልቀረሁ
                     እንደዛትኩ  ንደማልኩ  ንደተገዘትሁ
                     አንድ ቀን ተሳክቶ
                    መርበርበዴ  ቀርቶ
                    የልቤን የዉስጤን  አንበልብየዋለሁ
                    የመጨረሻዉን  አንድ አረፍተ -ነገር  ተንፍሼላታለሁ
                    ብያለሁ ብያለሁ ኔስ ደፍሬአለሁ
                    "ምንም ብታደርግኝ ኔ  ወድሻለሁ"
                    አይኗ አይኔን ያየዉ ሌላ ምን ላለሁ።

ደግሞም ስንለያይ  በራሴ ያፈርኩ
በአጉል  ጉራዬ  ለራሴ የበሸቅሁ
ለህሊናዬ መልስ ምክንያት  ፍለጋ
ጄን ያፋተግሁ ሳዘግም ሳወጋ 
                   አይኗ አይኔን ባያየዉ እነግራት ነበረ  ብዬ  ታበያለሁ
                   አልፈራም ነበረ  ባታስለመልመዉ  ባታንከባልለዉ 
                                                     ብዬ  እፀፀታለሁ:: 
   

ግና  ብትጨፍን  አይኗን ብትከድነዉ
ተሳክቶልኝ  ለአፍታ  አይኗ አይኔን ባያየዉ
እንኳንስ ልሳደብ እንኳንስ ላማርር
አሸናፊነቱ  አስበርጋጊነቱ ይለኛል ቅርቅር::    
   




                                   ታህሳስ  1  2006
                                    አዲስ  አበባ

                                    እዮብ  መርሻ





               

Monday, December 2, 2013

"ታምኝኝ ይሆን ...............????"

ጭንቅ ጥብብ ቅትትት
እብድ    ክንፍ ሙትትትት
ሰዉነቴ ጥቁር  ክስት
የአልታይነት  እልም ጥፍት
ሳቅ ጨዋታ  ቅርት ትዉት
በእንቅልፍ  ማጣት  አይኔ ክርትት
ማሰብ ትቼ  ስለትምህርት
                        ባንቺ መዉደድ  ባንቺ  ፍቅር
                         ንብዝብዝብዝ  ስክርክርክር
                         ድብን  ቅጥል  እርርርርርር
                         አልኩኝ  ብየ  ባወራልሽ
                        ታምኝኝ  ይሆን  እዉነት  መስሎሽ????
ግን  ለእኔ  ፍቅር  መቼ  ይሄ ሆኖ
ሀዘን ጭንቀት ባንቺ  ሀሳብ  ተሸፍኖ
አእምሮዬ  ነቅቶ  ባንኖ
የሚያስደስት       የሚያረካ
የሚያዎፍር        የሚያፈካ
የሚያኮራ          የሚያስመካ
ወኔ  ሰጥቶ        እሚያነሳሳኝ
በአላማየ          እያጸናኝ
አዲስ ተስፋ      አስነግቦኝ
ልዩ  ደስታን      የሚቸረኝ
ያንቺ  ፍቅር  ጤና  እንጂ
መቼ  ለእኔ  ህመም  ሆነኝ!!!።

                               1998፥ ሐረር
                              እዮብ መርሻ  እና  ዉብሸት  አሰፋ

                  

Friday, November 29, 2013

ግን ታስታዉሺያለሽ ???



ግን   ታዉቂልኛለሽ ???
ግን  ታስታዉሺያለሽ ???
                  በዚያ  በቁር  አየር
                  አጥንት  በሚሰማ     በሚያንዘፈዝፍ   ብርድ
                  ከቅዝቃዜዉ  ብዛት   አግሬ  ምንም   ቢዝል 
                                            አግርሽ  ምንም   ቢርድ፣ 
                  ደከመኝ  አላልኩም   ደከመኝ  አላልሽም
                  አመመኝ  አላልኩም   አመመኝ  አላልሽም
                  የተቀመጥንበት ቢቀዘቅዘንም  ቢቆረቁረንም 
                  ምቾት  ቢነሳንም  አላለያየንም  
                  አቅፌሽ   አቅፈሽኝ     ረጅም ሰዓታት 
                                                 አብረን  ተቀምጠናል 
                                                 አብረንም  ቆመናል ፣
                  ካለንበት ቦታ    አዚሁ ቁጭ በለን  
                                                 በስሜት  መጥቀናል
                  በአንዳች  ልዩ ስሜት   ዋኝተናል  ቀዝፈናል !!!::

ግን   ታስቢዋለሽ ???
ግን   ታስታዉሻለሽ ???
                         በአኩለ  ሌሊት    በሚያስፈራ  ግርማ 
                         በምያፏጭ  ንፋስ  በድቅድቅ  ጨለማ 
                         ከጅብ አስደንጋጭ  ደምጽ   ከቀበሮ  ጩሀት
                         ከዉሾቹ  ስርያ  ከሀማዎች  ፉጨት
                         ከአግረ  ደረቅ ኮቴ   ከሰዎች  ሹክሹክታ
                         ሩቅ  ካለዉ ወሬ  ከሳቅ  ከሁካታ
                         ከዛፎች  ዝማሜ  ከንፋስ  ሽዉታ
                                                ከቅጠል  ኮሽታ
                         አኔን  የተሰማኝ  የልብሽ  ትርታ !!!::


ግን ታስታዉሻለሽ ???
ግን   ትረጅኛለሽ ???
                         ከአገር ምድሩ  ሁሉ  ከአየሩ መአዛ 
                         ሳር  ቅጠሉ  ሳይቀር   ያለው በየታዛ 
                         አጅግ ከማይመስጥ  ከሽንት  ቤት  ፍሳሽ 
                                                        ከቆሻሻ  ቦታ 
                        አጅጉን  ይግረምሽ  
                        አጅጉን  ይድነቅሽ
                        ደግሞም   ከሚያዉደዉ  ከአበቦቹ   ሽታ 
                        አኔን  የተሰማኝ   የአንገትሽ  ስር  ሽታ !!!::



ግን  ታዉቂልኛለሽ ???
ገን  ታስታዉሻለሽ ???
                         ርግጥ  ነዉ  ይበርዳል   አጥንትን  ይሰማል 
                         ሌላዉ   ሰዉ  ደራርቦ   ከንፈሩ  ይርዳል 
                         አጁን  ኪሱ   ከቷል   ጥርሱንም  ያፋጫል  
                         ታዉቂያለሽ  አኔ  ግን   በቅጡም  አለበስኩ 
                                             አንደ  ሰዉ   አልደረብኩ 
                        ግን  አኔ  ግያለሁ   በጣሙን   ሞቂያለሁ 
                        አንደ   ግንቦት  ፀሐይ  አጅግ   አፋጃለሁ 
                        ለምን  አንደሆነ  ታዉቂያለሽ  አዉቃለሁ 
                        ስለነበረ  ነዉ  ከዚያ  ሁሉ  ስሜት 
                        አኔን  የተሰማኝ  የአንገትሽ  ስር ሙቀት 
                                              የደም   ስርሽ  ዑደት
                                                  የደረትሽ  ግለት!!!::

       

ግን   ታስታዉሻለሽ ???
ግን  ታዉቂልኛለሽ ??? 
                                 ምን   አጅግ  ቢጨልም
                                 ለአይን  ባይታይም
                                 አካልሽ  ከአካሌ  በቃላት በድምፀት  ባይነጋገሩም 
                                 ጣቶችሽ   ጣቶቼን  ፈልገዉ  አያጡም 
                                 ከንፈርሽ   ከንፈሬን  ትንሽ  አንኩዋ  አይስትም !!!::



ግን  ታስታዉሻለሽ ???
ግን   ታዝኝልኛለሽ ???
                                   የድምፄን   መሻከር   የስትንፋሴን  ድክመት 
                                   የአፌን   መንተባተብ  አጥረቴን   ከቃላት 
                                   የከንፈሬን  መራድ   የትንፋሼን   ሙቀት 
                                   የአይኔን   መስለምለም  ድክምክም  ማለት ::



                  ምን  ታስታዉሻለሽ   ምን  ትረጅኛለሽ 
                  ምን  ታዉቂልኛለሽ   ምን ታዝኝልኛለሽ
                  ከንፈሬ  አያዎራ  ከጋለዉ   አንገትሽ  
                  ደረቴ   አያዎጋ  ከጋለዉ ደረትሽ 
                  አጅሽ  በጄ  መሃል  በላብ  ተጠምቆብሽ 
                  ለአፍታ ለደቂቃ  ጊዜ  ቢያገኝ  አፍሽ 
                  ስወድህ ስወድህ ስወድህ   በማለት 
                                                   ትሸዉጅኛለሽ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!::




                                                                                           ህዳር ፣2006
                                                              አዲስ   አበባ 
                                                              አዮብ  መርሻ