"እኔ ፍቅር ላይ ነኝ,,,"
የወሬ ማድመቂያ አደረጉኝ አሉ
የኔን መዉደድ ማፍቀር ሲያነሱ ሲጥሉ
ከንቶኔ ከእከሊት ይሆናል እያሉ
ሲያጋቡኝ ሲያፋቱኝ ቀን ይመሻል አሉ
ሲበጠስ ሲቀጠል ሲነፈስ ሲበጠር
ሲቦካ
ሲጋገር
ስሜ እንዲህ የዋለዉ
ያለአንዳች
አይደለም ያለ ምክንያት
እሳት በሌለበት ጢስ ኧረ ከወዴት
አልክድም አልዋሽም አላልኩም ሀሰት
ይስሙትም ይወቁት ሁሉንም ይረዱት
ለምን ጊዜ ያጥፉ ለምንስ ያስቡት
በየወሬዉ መሃል ስሜን ለምን
ያንሱት
ስጋዬን ቀን ከሌት ለምንስ ያላምጡት
እውነት ነዉ ልክ ነዉ ኧረ አልተሳሳቱም
አዎ ፍቅር ላይ ነኝ ለማንም አልክድም
መቼም ከማትርቀኝ ከማትለወጥ
ከምትመጣልኝ ብቻዬን ስሆን
ከተቀመጠችዉ ከሀሳቤ ስር
ከቀዝቃዛዉ ደሜ ከልቤ ሰፈር
እኔ ፍቅር ላይ ነኝ “ከትዝታ” ጋር።
እኔ ፍቅር ላይ ነኝ “ከትዝታ” ጋር።
ህዳር 30 ፥2006አዲስ አበባ
እዮብ መርሻ
No comments:
Post a Comment