“አይኗ አይኔን እያየዉ᎐᎐᎐᎐᎐”
ቀጥራኝ ስጠብቃት የዉሃ ላይ ሽታ የሆነች እንደሆን
ስልኬን ሳታነሳ የቀረች እንደሆን
ከአከሌ ጋር ሆና አየናት ያሉኝ ቀን
ዝናብ የቋጠረ ደመና እመስላለሁ
የመጨረሻ ነዉ ዛሬስ በቃ እላለሁ
ያየሁባትንም የሰማሁትንም
ዘክዝኬ ዘክዝኬ አወራላታለሁ
ንዴቴን በሙሉ አውጣባታለሁ
አልያም ሰድቢያት ባለችበት ቆማ ትቻት አሄዳለሁ
ሁለተኛ አይንሽን አንዳላየዉ ብዬ አባርራታለሁ
ብዬ አደነፋለሁ !!!
ብዬ አገዘታለሁ !!!
ታዲያ ስትመጣ ስትቆም ከፊቴ
አይኗ ሲስለመለም አያየሁት ባይኔ
ችግሩ ከማን ነዉ ከሷ ነዉ ውይ ከኔ
ብዬ አጠይቃለሁ ከጋለዉ ስሜቴ እቆራረጣለሁ
ባጠመደኝ አይኗ ወኔዬ ተሰልቦ እበረግጋለሁ
ጥፋቱ የኔዉ ብዬ እመለሳለሁ።
ግን ምን አረገችኝ ምስኪን ናት ፣ ቆንጆ ናት
በዚህ ላይ ደግሞ ያለኔስ ማን አላት
ደግሞም የሰማሁት ያየሁት በሙሉ
እዉነት መሆኑንስ በምን አዉቃለሁኝ
እንድያዉ ነዉ ዝምብዬ እሷን የኮነንኩኝ
ብዬ እሞኛለሁኝ።
አዬ ድንፋታ አቴ አዬ መንቆራጠጥ
መንቸርጨር መቃጠል ማለት ቁጭ ብድግ
ለዚሁ ነዉ ለካ
አጇ አጄን ፈልጎ አስኪነካ
ጥርሷ በፈገግታ በጥልቅ አስኪፈካ
አይኗ ካይኔ ጋራ አስኪያወካ
ከንፈሯ ከንፈሬን አስኪሄድ ፍለጋ።
ታዲያ እንዲሁ አልቀረሁ
እንደዛትኩ እንደማልኩ እንደተገዘትሁ
አንድ ቀን ተሳክቶ
መርበርበዴ ቀርቶ
የልቤን የዉስጤን አንበልብየዋለሁ
የመጨረሻዉን አንድ አረፍተ -ነገር ተንፍሼላታለሁ
ብያለሁ ብያለሁ እኔስ ደፍሬአለሁ
"ምንም ብታደርግኝ እኔ ወድሻለሁ"
አይኗ አይኔን እያየዉ ሌላ ምን እላለሁ።
ደግሞም ስንለያይ በራሴ እያፈርኩ
በአጉል ጉራዬ ለራሴ እየበሸቅሁ
ለህሊናዬ መልስ ምክንያት ፍለጋ
እጄን እያፋተግሁ ሳዘግም ሳወጋ
አይኗ አይኔን ባያየዉ እነግራት ነበረ ብዬ እታበያለሁ
አልፈራም ነበረ ባታስለመልመዉ ባታንከባልለዉ
ብዬ እፀፀታለሁ::
ግና ብትጨፍን አይኗን ብትከድነዉ
ተሳክቶልኝ ለአፍታ አይኗ አይኔን ባያየዉ
እንኳንስ ልሳደብ እንኳንስ ላማርር
አሸናፊነቱ አስበርጋጊነቱ ይለኛል ቅርቅር::
ቀጥራኝ ስጠብቃት የዉሃ ላይ ሽታ የሆነች እንደሆን
ስልኬን ሳታነሳ የቀረች እንደሆን
ለመልዕክቴ
ምላሽ የነፈገችኝ ቀን
ደግሞም አግር ጥሎኝ በአይኔ በብረቱ
ከሌላ ጎበዝ ጋር ያየሁአት አንደሆን
እንገበገባለሁ እብከነከናለሁ
የመከዳት ስሜት የመከፋት ስሜት
በፊቴ አሳያለሁ
ፊቴ ተኮማትሮ
ከሰል መስሎ ጠቁሮዝናብ የቋጠረ ደመና እመስላለሁ
ብቻዬን አጉተመትማለሁ
ጨርቁን እንደጣለ እንዳበደ ሰዉ
እጄን ወዲያ ወዲህ አወረጫጫለሁ
ቆይ ትምጣልኝ ብዬ እጅግ እዝታለሁ
እጄን በእጄ ቡጢ
ደግሜ ደግሜ ደግሜ እመታለሁ::
ብርሃኑ ቀኔ በእሷ ጨልሞብኝ
እሸሽበት መንደር
እገባበት ጉድጓድ እጠፋበት ሰፈር፣
ካሳቤ ጠፍቶብኝ
ደግሞም ቅናት ቢጤ እያንጨረጨኝ
ደም
ደም አሸትቶ እያቀጣጠለኝ
ሃሳብ ሆዴ
ገብቶ እያብከነከነኝ፣የመጨረሻ ነዉ ዛሬስ በቃ እላለሁ
ትምጣና
እምላትን እኔ አዉቅላታለሁ
የት ነበርሽ?? ከማን ጋር?? እያልኩ አጣድፋታለሁ
ከእግሯ እስከ ራሷ እወርድባታለሁ
እንዲህ ነሽ እንዲያ ነሽ እያልኩ
እላታለሁያየሁባትንም የሰማሁትንም
ዘክዝኬ ዘክዝኬ አወራላታለሁ
ንዴቴን በሙሉ አውጣባታለሁ
አልያም ሰድቢያት ባለችበት ቆማ ትቻት አሄዳለሁ
ሁለተኛ አይንሽን አንዳላየዉ ብዬ አባርራታለሁ
ብዬ አደነፋለሁ !!!
ብዬ አገዘታለሁ !!!
ታዲያ ስትመጣ ስትቆም ከፊቴ
አይኗ ሲስለመለም አያየሁት ባይኔ
ችግሩ ከማን ነዉ ከሷ ነዉ ውይ ከኔ
ብዬ አጠይቃለሁ ከጋለዉ ስሜቴ እቆራረጣለሁ
ባጠመደኝ አይኗ ወኔዬ ተሰልቦ እበረግጋለሁ
ጥፋቱ የኔዉ ብዬ እመለሳለሁ።
ግን ምን አረገችኝ ምስኪን ናት ፣ ቆንጆ ናት
በዚህ ላይ ደግሞ ያለኔስ ማን አላት
ደግሞም የሰማሁት ያየሁት በሙሉ
እዉነት መሆኑንስ በምን አዉቃለሁኝ
እንድያዉ ነዉ ዝምብዬ እሷን የኮነንኩኝ
ብዬ እሞኛለሁኝ።
አዬ ድንፋታ አቴ አዬ መንቆራጠጥ
መንቸርጨር መቃጠል ማለት ቁጭ ብድግ
ለዚሁ ነዉ ለካ
አጇ አጄን ፈልጎ አስኪነካ
ጥርሷ በፈገግታ በጥልቅ አስኪፈካ
አይኗ ካይኔ ጋራ አስኪያወካ
ከንፈሯ ከንፈሬን አስኪሄድ ፍለጋ።
ታዲያ እንዲሁ አልቀረሁ
እንደዛትኩ እንደማልኩ እንደተገዘትሁ
አንድ ቀን ተሳክቶ
መርበርበዴ ቀርቶ
የልቤን የዉስጤን አንበልብየዋለሁ
የመጨረሻዉን አንድ አረፍተ -ነገር ተንፍሼላታለሁ
ብያለሁ ብያለሁ እኔስ ደፍሬአለሁ
"ምንም ብታደርግኝ እኔ ወድሻለሁ"
አይኗ አይኔን እያየዉ ሌላ ምን እላለሁ።
ደግሞም ስንለያይ በራሴ እያፈርኩ
በአጉል ጉራዬ ለራሴ እየበሸቅሁ
ለህሊናዬ መልስ ምክንያት ፍለጋ
እጄን እያፋተግሁ ሳዘግም ሳወጋ
አይኗ አይኔን ባያየዉ እነግራት ነበረ ብዬ እታበያለሁ
አልፈራም ነበረ ባታስለመልመዉ ባታንከባልለዉ
ብዬ እፀፀታለሁ::
ግና ብትጨፍን አይኗን ብትከድነዉ
ተሳክቶልኝ ለአፍታ አይኗ አይኔን ባያየዉ
እንኳንስ ልሳደብ እንኳንስ ላማርር
አሸናፊነቱ አስበርጋጊነቱ ይለኛል ቅርቅር::
ታህሳስ 1 2006
አዲስ አበባ
እዮብ መርሻ
No comments:
Post a Comment