ይቅርታሽን
እንዴት ሳላስቀይም እንዴት ሳላስከፋሽ
እንዴት ሳላስቀይም እንዴት ሳላስከፋሽ
ለቁጣ የሚያደርስ በደል ሳልበድልሽ
ለመጥፎ ነገር አንዴም ሳላስብሽ
ስምሽን ሳልጠራ ለሰዉም ሳላማሽ
ከልቤ
አዉጥቼ አፌ ሳላደርስሽ
የሚያስከፋ ነገር ቃል ካፌ ሳይወጣ፣
የሚያስከፋ ነገር ቃል ካፌ ሳይወጣ፣
ይቅርታሽን ብዬ አደባባይ ልዉጣ?
እንኳን ያጠፋ ሰዉ ፍቅርን የበደለ፥
ንጉስ ይቅር ይላል ፍርድ ካጓደለ፤
ስሜት የሚያስቆጣ የሚያስከፋ ነገር
በልቡ ያሰበ ካፉ ያመለጠዉ፥
ፍቅሩ እንዲሰነብት
ይቅርታ መጠየቅ ይሆናል ግዴታዉ፤
ጡር ይሁን
አልልም ጡር አይድረስብሽ
ግፍ
ነዉም አልልም ግፍ አይሁንብሽ
ልትዋሽ የማትችይዉ እዉነቱን የሚያዉቀዉ
ህሊናሽ ይዉቀስሽ።
ታህሳስ 1 2006
አዲስ አበባ
እዮብ መርሻ
እዮብ መርሻ