ከልጅነት ፍቅር ከነቂም አይዙ
ጥቅም
አይፈልጉ
ነግቶ አይጠገቡ
በሆነዉ ባልሆነዉ ካልሆነዉ ብስጩ
አለም ሁሉ ለእሱ ገነት ከምትመስለዉ
ትንሽ ትዝታ አለኝ በልቤ ቦታ አለዉ።
ደግሞም ከበሰለዉ ከሚያመዛዝነዉ
ይህ ይበልጥ ያ ይበልጥ ብሎ ከሚመርጠዉ
ለጊዜያዊ ስሜት ቅድሚያ ከሚሰጠዉ
ቆሻሻ ብስባሽ ሀጢያት ከለበሰዉ
ባፈቀረዉ ልብ ዉስጥ ቅናት ከሚረጨዉ
መክዳት መሸዋወድ ርስቱ ከሆነዉ
በከንፈር በደረት እንዲሁም በዳሌ ከሚፈራርሰዉ
ከአዋቂዎች ፍቅር ትንሽ ቀምሻለሁ።
ግን በአሁኑ ሰአት
በሃሳቤ ቀርጨ ስዬ ካስቀመጥኳት
ያለኝን ሁሉ ልሰጣት ላወርሳት ከምጠብቃት
ስተኛ ከጎኔ በትራሴ ምትክ ተኝታ ከማቅፋት
የግራ ደረቴን ከምትንተራሰዉ
የልቤ ትርታ ሙዚቃ ከሆናት
ጸጉሯን እያያሻሸሁ የኔነሽ ከምላት
ንጉሴ ስትለኝ ቀን ሌት ካነገስኳት
ማታ በጨረቃ ከደጅ ቁጭ ብዬ
ባሳብ የሳልኳትን የምወዳትን ልጅ
ከሃሳቤ አምጥቼ
ከጎኔ አስቀምጬ
ዘመም አርጋ አንገቷን አንገቴ ስር ገብታ
ሙቀቴን ሰጥቻት ሙቀቴን ፈልጋ
እየተደባበስን
በለሆሳስ ድምጸት እያንሾካሾክን
ፍቅር ስናወራ
ፍቅርን ስንበላ
በእጇ እየጠቆመች ሽቅብ ለጨረቃ
ዉዴ እወድሃለሁ ማሬ አፈቅርሃለሁ
እማኝ ወይ ምስክር ትሁነኝ ጨረቃ
ብላ ስታበቃ፤
እኔም ብዬ ሳልል ድምጽ ሳላወጣ
የፍቅሬን ጥልቀት የመዉደዴን ርቀት ልናገር ስቃጣ
ከምታስቸግረኝ ሙቀቷ ሳይለቀኝ አካሏ እየጠፋ፤
ደግሞም አመሻሽ ላይ በመንገድ እየሄድኩ
በእግሬ የድንጋይ ጓል ወደፊት እያጓንኩ
እጄ ኪሴ ገብቶ እየተንጎራደድኩ
በከፊል ብርሃን ዘንባባ እየታከኩ፤
ከወጪ ወራጁ ከተመላላሹ
ወይ የሚዋደዱ ወይ የሚወሻሹ
ላይሸዋወዱ የሚሸዋወዱ
በአርቴፊሻል መዉደድ በኮንትራት
ፍቅር የሚወላገዱ
ጥንዶች ያየሁ እንደሁ ተቃቅፈዉ ሲሄዱ
ያቺን ባሳብ ሸራ በመኞቴ ቀለም የሳልኳትን ወጣት
ወገቤን ጨምድዳ ስትይዘኝ አየኋት
ቀኝ እጄን በአንገቷ እያመላለስኩኝ
በርምጃችን መሃል ሰገፋት ስትገፋኝ
በወጋችን መሃል አንዳንዴ ስትመታኝ
ሂድ !!! ዉሸታም ስትለኝ
ለጊዜዉ አኩርፋ ወዲያዉ ስትስቅልኝ
ባሳቤ ሸራ ላይ እያለሁኝ ስያት
ከጎኔ ሳትኖረ ከልቤ አስቀምጫት
ምኞቴ ቀለሙ ሳያልቅ ሳይነጥፍ
እያመለጠችኝ እንደማትያዝ ወፍ
ሳላያት አሷን ሳላገኛት በዉኔ
አምላክ አደራህን አትለፍ ሂወቴ
ሳላያት አሷን ሳላገኛት በዉኔ
አምላክ አደራህን አትለፍ ሂወቴ
የማይሰጠኝ ከሆን የማይቸረኝ እሷን
ጌታ ጌትነቱ ፍቅር መቼ ሊሆን
እያልኩኝ እያሰብኩ
በቀን እየታመምኩ
እያየሁኝ
ቅዥት
ለምን እያፈቀርኩ አወራለሁ ዉሸት
ታህሳስ 6 2006
አዲስ አበባ