ሰልፍ በአገራችን በኢትዮጵያ ይዘቱ እና አላማዉ ይለያይ እንጂ ጥንትም እንደነበር በብዙ ደራሲያን ተፅፎ ይገኛል፡፡
ለምሳሌ ሰልፍ በእምየ ሚኒሊክ ዘመን ለሁለት አላማ ሲባል ይተገበራል፡፡አንደኛዉ ጦር ሰራዊቱ ወይም ወዶ ዘማቹ አገርን ከጠላት ወረራ ለመከላከል ወደ ጦር ግንባር ሲዘምት በራስ ተነሳሽነት በወኔ በፉከራ ፣ በሽለላ ፣ በቀረርቶ በመታጀበ የሚካሄደዉ ሰልፍ ሲሆን ፣ ሁለተኛዉ ደግሞ የቤተመንግስት ባለሙአሎች እና የንጉሱ አማካሪዎች ፣የጦር አለቆች ፣የቤተክህነት ሊቃዉንት ፣የህዝብ እንደራሴዎች ፣የጦር ሰራዊት አባላት ፣ተራዉ ህዝብ እና ሌላዉ ሌላዉም እንደየ ማዕረጉ ሆኖ (ተሰልፎ) በአጋፋሪዎች አስተባባሪነት ከንጉሱ ግብር ለመብላት የሚደረገዉ ስለፍ ነዉ ፡፡ይህ ሰልፍ እንግዲህ የሚደርገዉ በንጉሱ ፊት ተገኝቶ የማር ጠጅ ለመጠጣት ፣ጮማ ለመቁረጥ ፣የሊቃዉንቱን ቅኔ ዘረፋ ለመታደም ፣የአዝማሪን ጨዋታ ለማዳመጥ ወ.ዘ.ተ ሲሆን የጦር አለቆች እና ወታደሮች በፉከራ እና በቀረርቶ ንጉሱን ለማዎደስ እና ታማኝነትነን ለማሳየት አጋጣሚዉን ይጠቀሙበታል ፡፡ይህ እንግዲህ ሰባራ ሳንቲም የማይከፈልበት እና በንጉሱ ችሮታ ብቻ የሚከናዎን ነዉ፡፡ ከንጉሱ ግብር ለመካፈል የሚያስፈልገዉ ነገር ቢኖር እንደ መደቡ እና ማዕረጉ ተሰልፎ ወደ አዳራሽ መግባትና መግባት ብቻ ነዉ፡፡ ይህ እንግዲህ በአሁኑ ሰአት በየትኛዉም ቦታ የሌለ እና እንደ ተረት እየተወራ ያለ ጉዳይ ሆኖል፡፡
ከዚያም ወረድ እያልን ስንመጣ በጃንሆይ የንግስና ዘመን ሰልፍ ወራሪ ጦርን ለመከላከል እና ግብር ለመብላት መሆኑ ቀረና በአብዛኛዉ ለተቃዉሞ ወደ መሆን ተሸጋገረ ፡፡ በዚህም የተነሳ ህዝቡ እንደወትሮዉ ንጉሱ (ጃንሆይ) በተገኙበትም ሆነ በመንገድ ሲያልፉ ባለበት በየመንገዱ ዳር ተደርድሮ (ተሰልፎ) ለጥ ያለ ሰላምታ መስጠቱን ትቶ አገዛዙን ተቃዉሞ መፎክር ይዞ አደባባይ ወጣ፡፡ ይሄ ዘመን በአገራችን በኢትዮጵያ ታሪክ የተማረዉ ክፍል ለሀገሩ መቆርቆር እና የስልጣን ይገባኛል ጥያቄ ያነሳበት ጊዜ ነዉ፡፡ በዚህ የጎዳና ላይ ሰልፍ ባብዛኛዉ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ (የቀድሞዉ ቀዳማዊ ኀይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ) ተማሪዎች ንቁ እና ዋነኛ ተሳታፊዎችም መሪዎችም ነብሩ፡፡ ታሪከ ከማይረሳቸዉ የተቃዉሞ መሪዎች መካከል እንደነ ጥላሁንግዛዉ፣ ዋለልኝ መኮንን ፣ማርታ ( የዋለልኝ መኮንን የፍቅር አጋር) እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ ባለንበት ዘመን የምንኮንናቸዉም ሆነ የምናወድሳቸዉ አስመራሪዎቻችንም ሆኑ መሪዎቻችን እንዲሁም አገሪቱዋን በተለያየ አቅጣጫ የሚዘዉሩአት ሊቃዉንቶቻችን በሙሉ የዚህ ዘምን የሰልፍ ዉጤቶች መሆናቸዉን ልብይሉአል፡፡
ምን ያደርጋል ይህ ዘመን የተማሪዉ ተቃዉሞ ሀ ብሎ የተጀመረበትም ቢሆን በምላሹ የሰልፍ መሪዎችን እና ሰልፈኞችን ሂዎት መቅጠፍ የተጀመረዉ በዚሁ ዘመን ነዉ፡፡ የጥላሁን ግዛዉ፣
የዋለልኝ መኮንን እና ማርታ ሂወት ያለፈዉ በዚሁ ሰልፍ ነዉ፡፡እርግጥ ነዉ ፍቅረኛሞቹ ዋለልኝ እና ማርታ አዉሮፕላን ለመጥለፍ ሲሞክሩ ቢገደሉም ፤መነሻዉ በጊዜዉ የነብረዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ነዉ፡፡ የዚህ ዘመን ሰልፍ ዉጤቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ባብዛኛዉ ለዚህም ትዉልድ ተርፈዉታል፡፡ ሌላዉን ትተነዉ የነኝህ ሰልፎች የዚያን ጊዜ ገጽታ በብቸኛዉ ብሄራዊ ቴሌቪዥናችን ለተለያየ አላማ በተለያየ ጊዜ ለእኛ ለዚህኛዉ ዘመን ወጣቶች ባለንበት ይደርሰናል፡፡ በተለይ በተለይ የቀድሞዉ ቀዳማዊ ኀይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ተሰብስበዉ ለምን ለምን ሞተ ና ማርታ ለምን ሞተች የሚሉትን መፎክሮች በህብረት ሲያዜሙ መስማተ በጊዜዉ ለነበሩት ሰዎች ትዝታና ቁጭትን ሲያጭር ለእኛ ለአሁን ዘመን ወጣቶች የሚሰጠን ትርጉም የተለየ መሆኑ የማየቀር ነዉ፡፡ ወጣም ወረደ የዚህ ዘመን ሰልፍ አላማ በጊዜዉ የነበረዉን ጨቁዋኝ ንጉሳዊ አገዛዝ ከስልጣን በማዉረድ በምትኩ አለም ሲያቀነቅንለት የነበረዉን የሌኒን ህብረተሰባዊነት
(socialist, communist) የፖለቲካ ርዕዮተ-አለም (ideology) በኢትዮጵያችን ለመተግበር የተደረገ ትግል ነዉ፡፡
በንጉሱ ዘመን የተደረገዉ ሰልፍ የጊዜዉን ሰልፍ መሪዎች ሂወት ቢቀጥፍም የሁላ ሁላ አላማዉ ተሳክቶ ንጉሱን ከስልጣን አዉርዶ በምትኩ የህብረተሰባዊነት ፖለቲካ ርዕዮተ-አለም አቀንቃኝ የክርስትና ልጅ የሆነዉን ወታደራዊ አገዛዝ (ደርግ) በዙፋን ላይ አስቀመጠ፡፡ በዚህኛዉ የአገዛዝ ዘመን ደግሞ የሰልፍ አላማዉና ዉጤቱ እጅግ እየከፋ መጣ፡፡ በጉአድ ሌተናል ኮሎኔል መንግስቱ ኀይለማሪያም የስልጣን ዘመን አደባባዮች በወታደሮች እና በተለያዩ ጦር መሳሪያ ተሸካሚ ተሸከርካሪዎች ሰልፍ ተለወጠ (መስከረም ሁለት የሚከበረዉን የአቢወት ቀን ማስታወስ በቂ ነዉ)፡፡ ይህ እንግዲህ ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለዉን መፎክር ያስተናገደ ሰልፍ ነበር፡፡ይሁንና ወታደራዊ ደርግ ስልጣን ላይ የወጣበትን አላማ ስቶ የብዙሀኑን የተማረ ክፍል ይሁንታ ባለማግኘቱ እና ፓርቲዎች በህቡዕ በመደራጀታቸዉ ፤ደርግ ያለምንም ደም የሚልዉን እንጉርጉሮ ክዶ በምትኩ ነጭ ሽብር ፣ቀይ ሽብር በሚለዉ ዘመቻ ኢትዮጵያ በደም ጎርፍ ታጠበች፡፡ በዚህ የአገዛዝ ዘመን እንደ ንጉሱ ጊዜ አደባባይ ወጥቶ ለመቃወም የሚያስችል ህግም እድልም አልነበረም፡፡ ከበፊቱ በተለየ አገሪቱ በምታደርጋቸዉ የዉሰጥ እና የዉጭ እማያባራ ጦርነት የተነሳ ስልፍ ሁሉ ወታድራዊ መልክ ነበረዉ ይባላል፡፡ የአሁኑን ዘመን ስላማዊ ሰልፍ ልብ ባልልም የዚያን ጊዜ ዘመን ሰልፍ ግን ግራ እጅን ከፍ አና ዝቅ በማድረግ ይካሄድ ነበር ይባላል፡፡ መፎክር በግራ አጅም ይሁን በቀኝ እጅ ለእኔ ልዩነቱ አይታየኝም፡፡ እንግዲህ በዚህ ዘመን ነዉ የዚህ ጽሁፍ አላማ የሆነዉ የሰልፍ አይነት የተጀመረዉ፡፡ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ከተቃዉሞ እና ከድጋፍ ሰልፎች ባለፈ ተራን ለመጠበቅ አስገዳጅ ተራ(ሰልፍ)
የጀመረዉ፡፡
ደርግ በሚከተለዉ የኢኮኖሚ እና ፖለቲካ ስርአት የተነሳ በከተሞች ዉስጥ የነበረዉ ህዝብ የምግብ ሸቃጣ ሸቀጦችን ለማግኘት ሲል በየህብረት ሱቆቹ በር ላይ አያሌ ሰአቶችን በሰልፍ ማሳለፍ ጀመረ፡፡ ድርቅ ባጠቃችዉ የአገሪቱ ክፍሎች የነበረዉን ገበሬ ያለፍላጎቱ በግዳጅ ሌላ ቦታ (በአብዛኛዉ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል)
ለማስፈር አያሌ አድካሚ ሰልፎች አካሂዶል፡፡እጅግ የሚያሳዝነዉ የዚያን ጊዜ ሰልፍ ግን ሰዉን ወደ እስር ቤት አና ከስርቤት ወደ እስር ቤት በሚወስዱበት ጊዜ የሚካሄደዉ ነዉ፡፡ስዉ ያለጥፋቱ እና ወንጅሉ መታሰሩ ሳያንስ እንደ በግ በሰልፍ እየተነዳ ወደ ማጎሪያ ቤት መነዳቱ ያሳዝናል፡፡ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ እጅግ አስከፊዉ እና አሰቃቂዉ ሰልፍ የሚፈጸመዉ ጉድጉአዳቸዉን ቆፍረዉ በጉድጉአዳቸዉ ፊት በተደረደሩ (በተሰለፉ) ተረሻኞች ነዉ፡፡
ይህ እንግዲህ በአጠቃላይ በአገሪቷ የሚታየዉ ነባራዊ ሃቅ ነዉ:: እኔ እንግዲህ ብዙ ሺህ ጥራዝ ነጠቆች በየዓመቱ ከሚፈለፈሉበት አንድ አንጋፋ ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ነዉ የምማረዉ:: ስለዚህ በዚያም ስላለዉ የሰልፍ ዓይነት ለመናገር ረዳት አያስፈልገኝም:: ከላይ ባነሳኋቸዉ የሰልፍ ዓይነቶች ላየ እኔሙሉ በሙሉ የመሳተፍ ግዴታዉ ባይኖርብኝም ፤ ነገር ግን በተማርኩበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ በሚካሄዱት ሰልፎች ላይ ግን የመሳተፍ የዉዴታ ግዴታ ነበረብኝ::በዚያም ስላለዉ ሁኔታ ሳልጠቅስ ባልፍ ሃሳቤን የተጓደለ ያደርግብኛል::
እንግዲህ እኔ በምማርበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ የተሰለፍኩበትን ቀን ከመቁጠር፤ ሰልፍ ያልተሰለፍኩበትን ቀን መቁጠር ሳይቀለኝ አይቀርም:: በዚህ ግቢ በቆየሁባቸዉ አመታት ዉስጥ ሰልፍ ያልተሰለፍኩት ለመተኛት፣ከግቢ ለመዉጣት እና በግቢዉ ዉስጥ ለመንቀሳቀስ ብቻ ነዉ ብል ያጋነንኩ አይመስለኝም።ከዚህ በተረፈ ማንኛዉም ተማሪ አዲስ ተማሪ ሆኖ( fresh man) ወደ ዩንቨርሲቲዉ ሲገባ ሻንጣ ለማስፈተሽ ከተሰለፈዉ ረጅም ሰልፍ አንሰቶ ፤ ወይ ተመርቆ ወይም ተባሮ( ተጭሮ) ከግቢዉ እስከሚለቅ ድረስ የማይሰለፍበት ቀን ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ:: ቀን በቀን ለመመገብ በየካፍቴሪያዉ ሰልፍ ፣ በየሴሚስተሩ ለመመዝገብ በየፋኩሊቲዉ እና በየዲፓርትመንቱ በር ላይ ሰልፍ ፣ በመዝናኛ ማእከላት (tv room) ኳስ ለማየት ሰልፍ ፣ ሻዉር ለመዉሰድ ሰልፍ፣ ወደ ፈተና አዳራሽ ለመግባት ሰልፍ፣የተበላሸ ዉጤት ለማስተካከል ሬጅስትራር በር ላይ ረጅም ሰልፍ፣ በመመገቢያ አዳራሽ ዉስጥ ሻይም ሆነ ዉሃ ለመቅዳት ሰልፍ፤ ቦታ ተገኝቶ በልተዉ ከወጡም በኋላ ቢሆንም እጅን ለመታጠብ መሰለፍ ግድ ነዉ።በሲኒማ ቤት ዉስጥ የሚታዩ ፊልሞችን ለማየት ከፈለጉም በብቸኛዉ የመመረቂያ አዳራሽ በር ላይ ከአንድ ሰዓት በላይ መሰለፍ የማይቀር መሆኑን አምነዉ መሆን አለበት። ከዚህ በመነሳት አንድ የዩንቨርሲቲ ተማሪ ለአንድ ቀንም ቢሆን ሰልፍ አልተሰለፍኩም ካለ አልተመገበም፣ አልጠጣም፣ ገላዉን አልታጠበም፣ በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስኳቸዉን ዩንቨርሲቲዉ የሚሰጠዉን አገሎት አልተጠቀም ማለት ነዉ።
ይህ የዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ ከመለመዱየተነሳ ተማሪን የሚያስጨንቅም ሆነ የሚያበሳጭ አይደለም። ተማሪዉ ሰልፉ እጅግ የበዛ መስሎ ከተሰማዉ ሰልፉ ቀለል የሚልበትን ሰአት ጠብቆ ለመምጣት ይገደዳል። በተረፈ የሰልፍ ሰዓቱን በ ወሬና በጨዋታ ለማሳጠር የሚጥረዉ ይበዛል። ከዚህ ሌላ አማራጭ የለዉም። ከተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ዉጭ ለመመገብ ቢያስቡም እዚያም ቢሆን ቆመዉ አይሰለፉ እንጅ ተራ መጠበቅ ያለ ነዉ።ይህ ሰልፍ ሳስበዉ ተማሪዉ ከዩነቨርሲቲ ተመርቆ ሲወጣ የሚጠብቀዉን የሰልፍ አይነት እንዲለምድ ታስቦ የሚሰጥ የሰልፍ ስልጠና ይመሰለኛል።
በተለይ በመመገቢያ አዳራሽ ሰልፍ ላይ በአንድ ወቅት አንድ ገጠመኝ አለኝ።የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለሁ፤ አንድ ስራ የሚበዛበት አስተማሪያችን ከጥዋቱ 12፡30 እስከ 2፡30 ሊያስተምረን ተስማማን፡፡ታዲያ በተስማማንበት ቀን ለመማር ወደ ክፍል ከመግባታችን በፊት ቁርስ ለመብላት ካፍቴሪያዉ በሚከፈትበት ሰዓት ( ከጠዋቱ 12፡00) በጣት የምንቆጠር የአንድ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ወደ ተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ (ካፌ) አመራን።ይህ እንግዲህ በአጠቃላይ በአገሪቷ የሚታየዉ ነባራዊ ሃቅ ነዉ:: እኔ እንግዲህ ብዙ ሺህ ጥራዝ ነጠቆች በየዓመቱ ከሚፈለፈሉበት አንድ አንጋፋ ዩንቨርሲቲ ዉስጥ ነዉ የምማረዉ:: ስለዚህ በዚያም ስላለዉ የሰልፍ ዓይነት ለመናገር ረዳት አያስፈልገኝም:: ከላይ ባነሳኋቸዉ የሰልፍ ዓይነቶች ላየ እኔሙሉ በሙሉ የመሳተፍ ግዴታዉ ባይኖርብኝም ፤ ነገር ግን በተማርኩበት ዩንቨርሲቲ ዉስጥ በሚካሄዱት ሰልፎች ላይ ግን የመሳተፍ የዉዴታ ግዴታ ነበረብኝ::በዚያም ስላለዉ ሁኔታ ሳልጠቅስ ባልፍ ሃሳቤን የተጓደለ ያደርግብኛል::

ይህ የዩንቨርሲቲ ዉስጥ ሰልፍ ከመለመዱየተነሳ ተማሪን የሚያስጨንቅም ሆነ የሚያበሳጭ አይደለም። ተማሪዉ ሰልፉ እጅግ የበዛ መስሎ ከተሰማዉ ሰልፉ ቀለል የሚልበትን ሰአት ጠብቆ ለመምጣት ይገደዳል። በተረፈ የሰልፍ ሰዓቱን በወሬና በጨዋታ ለማሳጠር የሚጥረዉ ይበዛል። ከዚህ ሌላ አማራጭ የለዉም። ከተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ዉጭ ለመመገብ ቢያስቡም እዚያም ቢሆን ቆመዉ አይሰለፉ እንጅ ተራ መጠበቅ ያለ ነዉ።ይህ ሰልፍ ሳስበዉ ተማሪዉ ከዩነቨርሲቲ ተመርቆ ሲወጣ የሚጠብቀዉን የሰልፍ አይነት እንዲለምድ ታስቦ የሚሰጥ የሰልፍ ስልጠና ይመሰለኛል።
በተለይ በመመገቢያ አዳራሽ ሰልፍ ላይ በአንድ ወቅት አንድ ገጠመኝ አለኝ።የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሳለሁ፤ አንድ ስራ የሚበዛበት አስተማሪያችን ከጥዋቱ 12፡30 እስከ 2፡30 ሊያስተምረን ተስማማን፡፡ታዲያ በተስማማንበት ቀን ለመማር ወደ ክፍል ከመግባታችን በፊት ቁርስ ለመብላት ካፍቴሪያዉ በሚከፈትበት ሰዓት ( ከጠዋቱ 12፡00) በጣት የምንቆጠር የአንድ ዲፓርትመንት ተማሪዎች ወደ ተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ (ካፌ) አመራን።
. ።።።።።።።።ይቀጥላል።።።።።።።።።።።።።።