ከነገሮች በፊት ድሮ አተም ነበረች
በጊዚዎች ሂደት አተም ተለጠጠች
በቢግባንግ ክስተት ዩንቨርስ ተፈጠረች
ትንሽቷ አካል ይኅዉ አንዲህ ሆነች
ቢሊዮን ከዋክብት በዉስጧ ከተተች
አያሌ ፕላኔት አያሌ ጨረቃ አጠረቃቀመች
ይለኛል በሳይንስ አሱ በተማረዉ
ገባኝ አልገባኝ አሱ ምን ቸገረዉ
ማወቁን ማወቄ ከኔ አሚጠበቀዉ
ለአንደኔ አይነቱማ ሳይንስ ለራቀዉ
የመረጃ ርቀት የመረጃ ጉድለት ለማያስጨንቀዉ
ከሆዱ በስተቀር ግድ ለማይሰጠዉ
የከርሱ መገቸር አርካታዉ ለሆነዉ
በዋዛ ፈዛዛ ጊዜ ለሚገድለዉ
አተም የጤፍ ዱቄት
ዩንቨርስም ቡሃቃ
ቢግባንግም ኩፍታ
መሆኑን ቢረዳ
ኧረ አንደምን ብሎ በሳቅ በፈነዳ::
ጥር 2001 አዲስ አበባ
አዮብ መርሻ
በጊዚዎች ሂደት አተም ተለጠጠች
በቢግባንግ ክስተት ዩንቨርስ ተፈጠረች
ትንሽቷ አካል ይኅዉ አንዲህ ሆነች
ቢሊዮን ከዋክብት በዉስጧ ከተተች
አያሌ ፕላኔት አያሌ ጨረቃ አጠረቃቀመች
ይለኛል በሳይንስ አሱ በተማረዉ
ገባኝ አልገባኝ አሱ ምን ቸገረዉ
ማወቁን ማወቄ ከኔ አሚጠበቀዉ
ለአንደኔ አይነቱማ ሳይንስ ለራቀዉ
የመረጃ ርቀት የመረጃ ጉድለት ለማያስጨንቀዉ
ከሆዱ በስተቀር ግድ ለማይሰጠዉ
የከርሱ መገቸር አርካታዉ ለሆነዉ
በዋዛ ፈዛዛ ጊዜ ለሚገድለዉ
አተም የጤፍ ዱቄት
ዩንቨርስም ቡሃቃ
ቢግባንግም ኩፍታ
መሆኑን ቢረዳ
ኧረ አንደምን ብሎ በሳቅ በፈነዳ::
ጥር 2001 አዲስ አበባ
አዮብ መርሻ
No comments:
Post a Comment